Ebakesh Tarekign
Madingo Afework Lyrics


ተንገበገበልሽ አረረልሽ ሆዴ
አትራቂኝ በኔ ሞት አይብዛ መንደዴ
ያስታርቀን መውደዴ

ልመናዬን ስሚ ይቅርታሽ ይድረሰኝ
ጥፋቴን ለመርሳት እኔ አቅም አነሰኝ
ልቤ እየወቀሰኝ

ከትዝታሽ ንዳድ አልዳነም አንጀቴ
አንቺን ካጣሁ ወዲህ ተጨንቋል ስሜቴ
አልበላም አልጠጣም እምቢ እያለኝ ሆዴ
በይግባኝ ሳይታይ ሊቀር ነው ወይ ፍርዴ

የእድሜን ጠዋት ማታ በትካዜ ገፋው
አጣሁት ሰላሜን አንቺን ስላስከፋው
ያለውን ችያለው መጪው ካልከበደኝ
ጸልይልኝ ፍቅርሽ እንዳያሳብደኝ

ላንቺ ይብላኝ እንጂ አልል አልተመቸኝ
ላንቺ ይብላኝ እንጂ አልል አልተመቸኝ
እወዳታለው ማለት አይሰለቸኝ
እወዳታለው ማለት አይሰለቸኝ

ተራዬን ብነሳ ልበር እንደ ግዴ
ብመርጠው መራቁን አይቀናኝ መንገዴ
ስቴጂ ቢከፋኝ ስሞታ አላሰማ
ተለየሽኝ ብዬ ዛሬ አንቺን አላማ

ክፉሽን አውርቼ አልኖርም ሲቆጨኝ
ቅናት ነው ጠላቴ የሚያነጫንጨኝ
ዳርእስከዳር ብዞር ልክሽን አላገኝ
ልርሳሽ ብል መንፈሴ ሰውም አያረገኝ

እምባዬን ባፈሰው አፍ ላይደቅንበት
የኔ ቃላት ናቸው ፍቅሬን የቀኑበት
አይኔን እየረሳሁ በዛፍ በቅጠሉ
ተብሰልሳይ አርጎኛል ካንቺ መነጠሉ
ትካዜን አጥምደው ምንም ቢፈዙበት
ያዩበታል እንጂ ወፍን አይዙበት

እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ
ተይ አታስጨንቂኝ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ
ተይ አታስጨንቂኝ

ልቦናሽ ከኔ አካል ሊርቅ መወሰኑ
ጠፍቶብሽ ይሆን ወይ የመቻል ወሰኑ
አንድም ጸጽቶኛል ለሱም በይኝ ይቅር
አይለመደውም ቅጣት ሰው ሲቀጣው ፍቅር

ልቦናሽ ከኔ አካል ሊርቅ መወሰኑ
ጠፍቶብሽ ይሆን ወይ የመቻል ወሰኑ
አንድም ጸጽቶኛል ለሱም በይኝ ይቅር
አይለመደውም ቅጣት ሰው ሲቀጣው ፍቅር

ኧ.ሀ... ሀ.ሀ... ኧ.ሀ.ሀ.ሀ

ምነው በትዝታ ሁሌ እንደምመኝሽ
ከጉጉቴ መረብ ተቀምጠሸ ባገኝሽ
እኔ አዳኝ አይደለሁ አላልም በጫካ
ምንሽሬ እምባ ነው ህልሜም ባይሳካ

ብዙ ማልቀስ ባዳም ባይለመድ እንኳን
ባንቺ ሀዘን ልቤ ላይ አስጥያለው ድንኳን
ብትባበርኝም ምድር ለአራት ታጥፋ
አብረን እንኑር እና እስኪ አምኜሽ ልጥፋ

ቀራንዮም ይስማ ጎሎጎታም ይወቅ
አይረዳን ምህረቱ እኛ ሳንታረቅ
ባይጻፍም ሰአት ለአለም መጨረሻ
ቀን ማጣት ምጻት ነው አንቺ መመለሻ

እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ
ተይ አታስጨንቂኝ
እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ
ተይ አታስጨንቂኝ

Writer(s): Simone Tsegay

Contributed by Mia R. Suggest a correction in the comments below.
To comment on specific lyrics, highlight them
Genre not found
Artist not found
Album not found
Song not found
Comments from YouTube:

Afom mobae

I am eritrean but I love it Ethiopian music

SMARt

Rip madingo rest in peace

Roman Getachew

I love it

ትዳር የኢማን ግማሽ ነዉ Altoupa

ትዝታ አለብኝ አልሀምዱሊላህ አሁን አብረን ነን

Naaaema Alln

እኔ ደሞ ገና በ14 አመቴ እማፈቅርው ልጅ አጎቴ ልጅ ላይ ያስኩትና ያስኩትና ለቤ ተሠበር አሁን ላይ ሁሉም ወድ እደዛው እየመሠለኝ መቅርብ አልቻልኩ አሁን 20 አመቴ ነው በልጅነት የተሠበረ ልብ መቸም አይጠገን ውድ እህቶቸ አሁን ግን ሥኡድ አረቤያ ከመጣሁ 2 አመቴ ነው ግን አሁንም ሠው ማመን አልቻልኩም ይሄን ሙዚቃ ስለጋበዘኝ አድ አድ ግዜ እየገባሁ እሰማዋለሁ ግን አልሀምዱሊላ ሁሉም ለበጎ ነው የተሠበረው ልቤ እድጠገን ዱአ አድርጉልኝ እናም ወድሞቸ የሴትን ልጅ ልብ አትሥበሩ በአሏህ በናተ ምክናየት ሰው እዳናምን አታድርጉን

Zd bint Dad

ተንገበገብኩለ፯ህ አረረ ልህ ልቤ😢😢😭😭

Merete Mengesha

እስከ መጨረሻው እምባዬ ሊቆም አይችልም ስለ
ሞተ አይደለም የማደንቀው VA USA sky lion አግኝቼው በጣም እንደማደንቀው ነግሬዋለሁ።
ነፍስ ይማር።

kalkidan Tesfaye

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

Cell Center

Wwwwwwffffffff♥️♥️♥️♥️♥️♥️

نوح الدين

👍👍👍👍

More Comments

More Videos